ESAT Radio Wed 22 Jun 2016

ኢሳት ሬዲዮ
-በሻሸመኔ ባልታወቀ ምክንያት ሰዎች እየተገደሉ ነው። ባለፉት ቀናት ከ8በላይ ሰዎች በተመሳሳይ አገዳደል ሞተው መገኘታቸው ነዋሪውን ስጋት ላይ ጥሏል።
-የኢትዮጵያ የብድር መጠን ጣሪያውን ሊነካ ነው። 36 ቢሊየን ዶላር እስከ 2015 ድረስ የተበደረው መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
-በኮንሶ ውጥረቱ ተባብሷል። ነዋሪው ሲቪል አስተዳደር የለም። በወታደር ተተክቷል ብለዋል። ሰዎች ታፍነው እየተወሰዱ ነው።
-የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት አባል አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቀለች። ሜሮን ዓለማየሁ ሰላማዊ ትግል በቃኝ ብላለች።
-ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት በወሳኝ ሀገራት አምባሳደሮችን በህወሀት አባላት እየተካ ነው። ምክንያቱ በግልጽ አልታወቀም።