Home » የኢሳት አማርኛ ዜና » የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ:: በተለይ የቴሌኮም ዘርፉ ለከፍተኛ  ሙስና የተጋለጠ መሆኑን አስታወቀ::

ባለፈው አርብ በአለም ባንክ ይፋ የተደረገ ሪፓርት እንዳመለከተው በተለይ በግዥና በአቅርቦት ሂደቶች የሚታዩት ክፍተቶች ለሙስና አደጋ በመጋለጥ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን ሪፓርቱ አመልክቶል::

የሀገሪቱን የሙስና መጠን ላለፉት ስድስት ወራት ሲያጠና የቆየው የአለም ባንክ በተለይ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች ብሎ በመደባቸው

ንዑሳን ክፍሎች ውስጥ የተካተቱት ቴሌኮም፣ የኤች አይ ቪ መከላከልና ህክምና የመድሀኒት ዘርፉን ጨምሮ በሙስና ቀለበት ውስጥ የወደቁ ናቸው ብሎል::

በመሰረታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቆማት ብሎ ባንኩ በመደባቸው ትምህርት፣ ጤና፣ ፍትህና የመሳሰሉት ተቆማት ቀላል የማይባል ሙስና የሚታይባቸው መሆኑን አጋልጦል::

ባንኩ ያፋ ባደረገው በዚ ሪፓርት ከፍተኛ ሙስና ከሚታይበት ከቴሌኮም ኢንዱስትሪ ቀጥሎ መሬትና ኮንስትራክሽን ዘርፉ በሙስና መዘፈቁን ይፋ አድርጎል::