Home » የኢሳት አማርኛ ዜና » በኢትዮጵያ በደን የተሸፈነ መሬት ከ 40 በመቶ ወደ 2፡4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ

በኢትዮጵያ በደን የተሸፈነ መሬት ከ 40 በመቶ ወደ 2፡4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በቢዝነስ ዜናዎች ላይ እያተኮረ አዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ሀገሪቱ 37፡6

ከመቶ ደኖን አታለች::

በሀገሪቱ ያለው እንጨትን በማገዶነት የመጠቀም ፍጆታ በአመት 50 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያመለከተው ይህ ዘገባ የደን መጨፍጨፍ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ ጠቅሶታል::

ይህም ሀገሪቱ ከምትጠቀመው አጠቃላይ ሀይል 80 ከመቶውን ከእንጨትና ከእንጨት ውጤቶች መሆኑ በዘገባው ተመልክቶል::

በኢትዮጵያ በደን የተሸፈኑ መሬቶች ተጨፍጭፈው በርካሽ ዋጋ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሸጡ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል:፡