Home » የኢሳት አማርኛ ዜና » በመከላከያ ሰራዊትና በሱሪዎች መካከል የተካሄደው ግጭት ቀጥሎ 3 ሱሪዎች መገደላቸው ታወቀ

በመከላከያ ሰራዊትና በሱሪዎች መካከል የተካሄደው ግጭት ቀጥሎ 3 ሱሪዎች መገደላቸው ታወቀ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በሱሪዎችና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተነሳ ግጭት 3 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል።

በግጭቱ በርካታ የሱሪ ከብቶች መገደላቸውን ለማወቅ  ተችሎአል።

ባለፈው ቅዳሜ በአካባቢው ግጭት ተነስቶ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።