Home » የኢሳት አማርኛ ዜና » በአለማጣ ከታሰሩት መካከል የተወሰኑት ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል

በአለማጣ ከታሰሩት መካከል የተወሰኑት ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል

ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም ከ 20 ያላነሱ ሰዎች ታስረው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።

አብዛኞቹ ወጣቶች ወደ ማይጨው እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸው ታውቋል። ከታሰሩት መካከል አቶ አባተ ያለው እስከ ልጃቸው፣ አቶ አሰፋ ዳርጎ ከሴት ልጃቸው ጋር ፣  ሽበሺ አለሙ፣  አሰፋ አሰግድ ፣  ውዱ ቸኮል፣ አቶ ዝናቡ ቸኮል ከሴት ልጃቸው ጋር እንዲሁም አቶ ፋንታ መሰለ ይገኙበታል። አቶ ፋንታው መሰለ እና ሌሎች ሶስት ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።

በርካታ የአካባቢው ወጣቶች ወደ ተለያዩ አካባቢዎች መሄዳቸው ታውቋል