Home » የኢሳት አማርኛ ዜና » አንድ የባለራእይ ወጣቶች የአመራር አባል ተይዛ ታሰረች መርፌ እንደተወጋች ተገልጿል

አንድ የባለራእይ ወጣቶች የአመራር አባል ተይዛ ታሰረች መርፌ እንደተወጋች ተገልጿል

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራር ጸሀፊ የሆነችው ወ/ት ወይንሸት ተይዛ የታሰረችው ትናንት ሲሆን፣ ዛሬ የስራ ባልደረቦቿ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ቃሉዋን እንድትሰጥ ለማድረግ ቢሞክሩም ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሊሳካላቸው አልቻለም። ወጣቷ መርፌ እንደተወጋች እና ቃሊቲ አካባቢ ከአንድ ክፍል ውስጥ መገኘቷን የማህበሩ ምክትል ሊቀመንበር ወጣት ሚካኤል ለኢሳት ተናግሯል

ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት ወ/ት ወይንሸት ለፖሊስ ቃሉዋን ሰጥታ ስትወጣ አነጋግረናታል። በቃለምልልሱ በኤሌክትሪክ ቶርች መደረጓንና ስቃይ ሲፈጸምባት ማደሩዋን በተዳከመ ደምጽ ተናግራለች።

ማህበሩ የፊታችን ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ ስብሰባ መጥራቱ የታወሳል።