Home » የኢሳት አማርኛ ዜና » አርቲስቶች በየካቲት ወር ለሚከበረው የመከላከያ ቀን ቅስቀሳ ጀመሩ

አርቲስቶች በየካቲት ወር ለሚከበረው የመከላከያ ቀን ቅስቀሳ ጀመሩ

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በአርቲስ ሰራዊት ፍቅሬና ሙሉአለም ታደሰ የሚመራው ግብረሀይል ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከቲያትሪካል አርት ተማሪዎች ገር ተገናኝቶ ስለመከላከያ ቀን አከባበር ውይይት ማድረጉ ታውቋል።

የኔነሽ ወልደገብሬልና ሌሎችም አርቲስቶች በስፍራው መገኘታቸውን የዩኒቨርስቲ ዘጋቢያችን ገልጿል።

አርቲስቶች በቅርቡ የአትዮጵያ አየር ሀይልን ጨምሮ የመከላከያን ኢንጂነሪንግን እንዲጎበኙ መደረጋቸው ይታወቃል። የጉብኝቱ አላማ አርቲስቶቹ በመጪው የመከላካያ ቀን በአል አከባበር ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ታስቦ የተደረገ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ከ98 በመቶ በላይ በአንድ ብሄር አመራር ስር እንዲሆን ተደርጎ መዋቀሩ በእየአቅጣጫው ተቃውሞ ትችት እያስነሳ እንደሚገኝ ይታወቃል።