Home » የኢሳት አማርኛ ዜና » በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወጣቶች ከፍተኛ የሆነ የነጻነት ተጋድሎ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑ ታወቀ

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወጣቶች ከፍተኛ የሆነ የነጻነት ተጋድሎ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑ ታወቀ

መጋቢት 17 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በዚህ ወር መግቢያ ላይ የኔሰው ገብሬን ለመዘከር በተካሄደው ስነስርአት ላይ በርካታ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት እንቅስቃሴ የተሳካ ዝግጅት ለማድረግ መቻላቸው ታውቋል። በዝግጅቱ ላይ የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች ሊግ ተወካይ በአካል ፣ የግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ እና ታዋቂው አርቲስት እና ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ታማኝ በየነ በስልክ ንግግር አድርገዋል።
ወጣቶቹ ከ1997 ምርጫ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን አስተባባሪው ወጣት ሙሉጌታ ፈለቀ ገልጧል ። የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከሁለት ቀን በፊት የጠራው ስብሰባ በወጣቶች እንቅስቃሴ በተጠበቀው መጠን ሳይሳካ መቅረቱን ወጣት ሙሉጌታ ገልጧል።