ታህሳስ 8 ቀን 2004 ዓ.ም
ባለፈው የጥቅምት ወር መጨረሻ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ከህዳር እስከ ጥር ወር 2004 ዓ.ም የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ እንደሚያደርግ ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር። በህዳር ወር ለመጀመር የታሰበው ዘመቻ ከዝግጅቱ ጋር በተዛመዱ የተለያዩ ቴክኒካዊ ምክንያቶች ሳቢያ ወደ ጥር ወር ለማስተላለፍ ተገዷል።
ከላይ በተጠቀሰው የጥቅምቱ መግለጫ ኢሳት በወቅቱ የነበረበትን ሁኔታ ገልፆ የነበረ ሲሆን፤ በዚህም፥ ኢሳት፤
አመላክቶ ነበር።
ከዚያም በኋላ ተከታታይነት ባለው መንገድ በወሰደው፤ ሥርጭቱን የማስፋት እና አገልግሎቱን የማጠናከር፤ ተግባር በአሁኑ ጊዜ ኢሳት፤
እነዚህ ዘርፈ ብዙ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በአግባቡ ለማከናወንም ሆነ በተከታታይነት እያጠናከሩ ለመቀጠል እንዲቻል የኢሳት የፋይናንስ አቅም በተጠናከረና አስተማማኝ መሠረት ላይ መቆም ይገባዋል። በዚህ ረገድ፣ ይህ በጥር ወር እንዲጀምር የታሰበው ዓለም-አቅፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ በታቀደው መሠረት ለማከናወን ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው።
በገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያው ዘመቻ ከተጠቀሱት አማራጭ የድጋፍ አይነቶች ውስጥ፤ ከላይ ለተጠቀሱት እንቅስቃሴዎች የሚያስፈልገውን ወጭ ለመሸፈን፣ ለአሰባሰብም ሆነ ለአጠቃቀም አስተማማኝና አመቺ ሆኖ የተገኘው፤ በየወሩ ከባንክዎ ወደ ኢሳት ባንክ በሚተላለፈው የቋሚ ክፍያ የሚደረገው ድጋፍ ነው። ይኸውም፣ በየወሩ ከባንክዎ ወደ ኢሳት ባንክ የሚተላለፈው የሂሳብ መጠን አሁን ኢሳት ባለበት የገንዘብ ወጪ አኳያ በትንሹ ከሃያ የአሜሪካ ዶላር ($20) ጀምሮ ሊሆን ይገባዋል። አቅምዎ የሚፈቅድ ከሆነ በወር ከተቀመጠው ዝቅተኛ ክፍያ ($20) በላይ በቋሚነት ኢሳትን ሊደግፉ ይችላሉ። ይህንንም ለማድረግ በቀጥታ በኢሳት ድረ-ገጽ ላይ ለዚሁ አመቺነት ተብሎ የተዘጋጀው ይህ ገጽ http://ethsat.com/Main/esat_recurring_monthly_donation.html በመጎብኘት ዛሬውኑ መተግበር ይችላሉ።
በተለያዩ ምክንያቶች ከባንካችሁ በቀጥታ በየወሩ ለኢሳት ድጋፍ ማድረግ ለማትችሉ ወገኖች በዚሁ በዓለም-አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ላይ ያቀረብናቸውን $100/£100/€100 ልዩ ቲኬት የምትችሉትን ያህል ብዛት በመግዛት ወገናዊ ግዴታችሁን መወጣት ትችላላችሁ። የቲኬት አቅርቦትን በተመለከተ የአካባቢዎን የኢሳት ተወካይ ለማግኘት እንዲችሉ በኢሳት ድረ ገጽ www.ethsat.com ላይ የተቀመጠውን የስልክ መረጃ መጠቀም ይችላሉ።
በመጨረሻም፣ ኢሳት በዚህ አጭር እድሜው ብዙ ፈተናዎች አጋጥመውታል። እነዚህ ፈተናዎች ቀላላ አልነበሩም። ፈተናዎቹን ለመወጣት ባደረገው ጥረት በቂ ተመክሮ አዳብሯል። ኢሳት ከፈተናዎቹ ያዳበረውን ልምድ በመጠቀምና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን ምንም ዓይነት ፈተና ማለፍ እንደሚቻል ሙሉ እምነት አለው። ለዚህም ነው ኢሳት የእያንዳንዱን ሃገርና ወገን ወዳድ ድጋፍ በመጠየቅ ለዕርሶም ጥሪውን የሚያቀርበው።
የኢሳት የነጻነት መንፈስ ለዘላለም ይኑር!!!
ኢሳትን መደገፍ ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ሀገራችንና ወገናችንን መታደግ ነው!!!
የኢሳት አስተዳደር
www.ethsat.com